fbpx

ኪንግደም ሪል እስቴት አርቲስት ጥላሁን ጉግሳን የብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሾመ!

ኪንግደም ሪል እስቴት የግሉ ሴክተር በሪል እስቴት ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦ በማድረግ የሚታወቅ ድርጅት ነው።

ኪንግደምሪልእስቴት በስራው አንቱታን ያተረፈውን አርቲስት ጥላሁን ጉግሳን ያለውን ተወዳጅነት እና ታማኝነት በማየት ለብራንድ አምባሳደርነት መምረጡን የሪል እስቴቱ ጀነራል ማናጀር አቶ ሚካኤል ወንደሰን ገልፀዋል።

አርቲስት ጥላሁን ጉግሳ በበኩሉ ብራንድ አምባሳደር በመሆኑ የተሰማውን ደስታ ገልፆ ኪንግደም ሪል እስቴትን ባለው ከፍተኛ ልምድ ለማስተዋወቅ ትልቅ ሥራ እንደሚሰራ ገልጿል።
በመስቀል ፍላወር ፣ ቦሌና ሰሚት ሳፋሪ በመገንባትና በመጠናቀቅ ላይ የሚግኙትን ቤቶቹን ለማስተዋወቅ የማስታወቂያና የኪነ ጥበባት ፕሮሞሽን መሥራች የሆነውን አርቲስት ጥላሁን ጉግሳ ዛሬ፣ ሐምሌ 12 ቀን 2015 ዓ.ም በእዮሜር ሆቴል በተካሄደ ሥነ ስርዓት የክብር አምባሳደር አድርጎ በክብር ሾመውታል።
የኪንግደም ሪል እስቴት ጀነራል ማናጀር የሆኑት አቶ ሚካኤል ወንደሰን እንደተናገሩት …
”ጥላሁን ጉግሳን የመረጥንበት ምክንያት በዘርፉ ላይ ረጅም ዓመት የሰራ፣ በሞያው ባለው ታአማኒነት እንዲሁም በሙያው ለታዳጊዎች ያለውን መሰጠት በማገናዘብ በዚህም የኪንግደም ሪል እስቴትን ዓላማዎች ይጋራል ብለን በማመናችን በክብር መርጠነዋል” ብለዋል።
አርቲስት ጥላሁን ጉግሳን በበኩሉ እንደተናገረው፥
”ታማኝ አድርጎ የመረጠኝን ኪንግደም ሪል እስቴት፥ እኔም ‘ኪንግደም ሪል እስቴት ምን ያህል ታማኝ ነው?’ የሚለውን አጣርቼ፥ ታማኝነቱን አረጋግጬ አብሬው ለመስራት ተስማምቻለሁ” ብሏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.