fbpx

100 ሺህ ቤቶች በ10 አመት!

በሚቀጥሉት 10 አመታት መቶ ሺህ የሚሆኑ ቤት ፈላጊ ነዋሪዎችን የቤት ጥያቄ ለመመለስ እንደሚሰራ ኬይ ሃውሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽንስ ፒኤልሲ ገለጸ፡፡
“Key housing finance solution plc” በሃገራችን የሚስተዋለውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመፍታት ለኗሪው ቀላል መንገድ ይዤ መጥቻለሁ ብሏል።
ድርጅቱ በሚቀጥሉት 10 አመታት ውስጥ የመቶ ሺህ የመኖሪያ ቤት ፈላጊ ነዋሪዎችን ፍላጎት እውን ለማድረግ መንገድ መጀመሩን አስታውቋል።
ድርጅቱ አሁን ላይ የጀመረው የቤት ሞዴል፣ አነስተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያለውን ቤት ፈላጊ ማህበረሰብ ታሳቢ በማድረግ የተጀመረ መሆኑ ተገልጿል።
አነስተኛ ገቢ ያላቸው ነዋሪዎች ከዚህ በፊት ባልተለመደ መልኩ በቀላሉ እና “በተዘዋዋሪ የቁጠባ ፈንድ “ሞዴል በባለቤትነት የሚረከቡበትን ቤት ክፍያ ይፈፅማሉ ተብሏል።
ይህ ክፍያ የሚፈፀው በዳሽን ባንክ የዝግ አካውንት ሲሆን፣ ድርጅቱ በተጨማሪም የቤት ክፍያ ሞዴልን ተአማኒነት ከፍ ለማድረግ ከቡና ኢንሹራንስ ጋር እየሰራ መሆኑንም ተናግሯል።
ቤት ፈላጊ ተመዝጋቢዎች በወር የዝግ የባንክ ሂሳብ 2ዐዐ0 ብር ተቀማጭ የሚያደርግ ሲሆን 230 ብር ደግሞ በተንቀሳቃሽ ሂሳብ የሚያስቀምጥ ይሆናል።
ቤቶቹ ተገንብተው ካለቁ በኋላ እንደቤቶቹ የካሬ ሜትር መጠን ልክ በ300 ሺህ እስከ 800 ሺህ ብር በክፈል ቤቶቹን እንደሚረከብ “key housing finance solution plc” አስታውቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.