fbpx

በአዲስ አበባ ከተማ የመሬት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ተጥሎ የነበረው ዕግድ ተነሳ!

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የመሬት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ፤ ከሐምሌ 28/2ዐ15 ጀምሮ ተጥሎ የነበረው ዕግድ መነሳቱ ተገለጸ፡፡
ዕገዳው የተላለፈው ቢሮው የሚሰጣቸውን አገልግሎቶችን የተቀላጠፈ ለማድረግ እንዲሁም፤ ከቢሮ ሪፎርም ሥራ ጋር በተገናኝ የሚስተካከሉ ሥራዎች በመኖራቸው መሆኑ ተገልጾ እንደነበር ይታወሳል፡፡
ይሁን እንጂ የዕገዳው መነሳት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ ከነሐሴ 8/2015 ጀምሮ ዕግዱ የተነሳ መሆኑን አዲስ ማለዳ በአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ቀነዓ ያደታ ተፈርሞ፤ ለኹሉም ክ/ከተሞች የመሬት ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት ከተላከው ደብዳቤ ተመልክታለች፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.