fbpx

በሪል እስቴት ግብይት ውል መካተት የሚገባቸው ጉዳዮች!

ቋሚ የዘርፉ ግብይት መመሪያ በሌለው የሪል እስቴት ግብይት ውስጥ በገዢና አልሚዎች መካከል የሚደረጉ ውሎች እጅግ በጣም የተለያዩ ናቸው። በዚህ ወቅት በግብይት ውስጥ መሬት የሌላቸው፣ የቤቱ ዲዛይን የማይታወቅ ( በካሬ ሜትር ብቻ እየተጠቀሰ) ፣ የማስረከቢያ ጊዜ ሳይገለጽ ፣ ፕሮጀክቱ ስለመተግበሩ ዋስትና የሚሆን ነገር ሳይኖር…ወዘተ ውል ተዘጋጅቶ ገዢና አልሚ እየተፈራረሙ እንደሆነ እየተመለከትን ነው።

ለግብይቱ ጤነኝነት ዋና ከሆኑ ጉዳዮች መካከል በተገበያዮች መካከል የሚደረግ ውል ይዘት አንዱ ነው በሪል እስቴት ግብይት ውስጥ ተዋዋይ ወገኖች ታሳቢ ሊያደርጓቸው የሚገቡ ሁኔትዎች በጥቂቱ እነሆ:-
1) የሁለቱ ተዋዋይ ወገኖች የተሟሉ መረጃዎች ( ስም ቋሚ አድራሻና ህጋዊ መረጃዎች)
2) ግብይት የሚፈጸምለት ቤት ዝርዝር መረጃዎች ( መገኛ ቦታው፣ የካርታ ቁጥር፣ የግንባታ ፈቃድ ቁጥር፣ የሚሸጠው ቤት ዲዛይን፣ የቤቱ መለያ ኮድ፣ የማጠናቀቂያ ቁሶች መረጃ …)። (ተገንብቶ ያለቀ ከሆነ ባለበት ይዞታ መሆኑን መግለ በቂ ነው)
3) የቤቱ ዋጋና የአከፋፈል ሁኔታዎች ዝርዝር ከክፍያ መንገዶችና የክፍያ መፈጸሚያ አካውንት ከማበረታቻ ቅናሾች እና ለዘገየ ክፍያ የሚቀመጡ ቅጣቶችን ጨምሮ መጠቀስ አለበት።
4) በአልሚው የሚመቻች የብድር አቅርቦት ካለ ከደንበኛው መቼ ምን እንደሚጠበቅበት በግልጽ ውሉ ውስጥ መቀመጥ አለበት።

5) ግንባታ ከመጀመሩ በፊት ቦታ መያዣ ወይም መተማመኛ ተብለው በዝግ አካውንት የሚከፈሉ ክፍያዎች ካሉ ምክንያቱና መጠኑ ተጠቅሶ መገለጽ አለበት

6) ፕሮጅክቱ የሚጠናቀቅበትና ገዢዎች ቤታቸውን የሚረከቡበት ቀን መጠቀስ አለበት

7) ከርክክብ በኋላ ለሚከሰቱ በግልጽ ያልታዩ የግንባታ ጉድለቶች እና በአጠቃቀም ሂደት ለሚከሰቱ አንዳድንድ ብልሽቶች የዋስትና የጊዜ ሰሌዳ መቀመጥ አለበት ( ይህ እንደ ሁኔታው ከአንድ እስከ ሁለት አመታት ሊሆን ሊበልጥም ይችላል)

8) የተናጠል ካርታ የሞሰጡበት ቀነ ገደብ መቀመጥ አለበት።

9) ከስመ-ሀብት ማዞር ጋር ተያይዞ ያሉ ወጪዎችንና ሰነዶችን ርክክብን በተመለከተ ዝርዝር የሃላፊነት መገለጽ ይኖርበታል

10) ውሉን በመተግበር ወቅት በሁለቱም ወገኖች ለሚገጥሙ የገቡትን ውልያለማክበር ስለሚፈታበት ሁኔታዎች መገለጽ ይኖርበታል።

ከላይ የተዘረዘሩት ጠቅለል ያሉ የይዘት ሁኔታዎች ጠቅለል ያሉ ታሳቢዎችን እንጂ ዝርር ሁኔታዎችን ያላካተቱ ሲሆኑ ተገበያዮች ከመገበያየታቸው በፊት ውሉ በሁለቱም ወገን ተቀባይነት ይኖረው ዘንድ ግልጽነት ኖሮት የህግ አማካሪዎችን አማክረው እንዲዋዋሉ ይመከራል።

In real estate transactions that do not have fixed sector marketing guidelines, the terms between buyers and developers are vastly different. At this time, we are seeing that those who do not have land in the market, the design of the house is unknown (only mentioned in square meters), the delivery time is not specified, there is no guarantee about the implementation of the project…etc.

The content of the contract between the traders is one of the most important issues for the transaction.
1) Complete information of the two parties (name, permanent address and legal information)
2) Details of the house to be sold (location, map number, construction permit number, design of the house to be sold, identification code of the house, information on finishing materials…). (If it is built and finished, it is enough to say that it is in possession)
3) The price of the house and the list of payment conditions should be mentioned, including payment methods and payment account, incentive discounts and penalties for late payment.
4) If there is a credit facility arranged by the developer, it should be clearly stated in the contract when and what is expected from the customer.

5) Before the start of construction, if there are payments to be made in a closed account as a deposit or trust, the reason and the amount should be mentioned.

6) The date on which the project will be completed and the buyers will take possession of their house should be mentioned

7) A warranty schedule should be provided for construction defects that are not clearly visible after delivery and for some malfunctions that occur during use (this may be longer than one to two years depending on the situation).

8) Date of submission of individual map should be fixed.

9) There should be a detailed description of the responsibility for the costs and the delivery of documents related to the transfer of assets.

10) During the implementation of the contract, it should be explained about the conditions for non-compliance with the contract that both parties will face.

The general content conditions listed above are general considerations and do not include detailed conditions. Before trading, it is recommended that traders consult with legal advisors to ensure that the contract is accepted by both parties.

Reference: Desalegn Real estate consultancy

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.