fbpx

አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ የቫሞስ ሪል እስቴት አምባሳደር ሆነ ፣ ለአንድ ዓመት 3.7 ሚሊዮን ብር ይከፈለዋል!

ቫሞስ ሪል እስቴት፣ አርቲስት ነጻነት ወርቅነህን የብራንድ አምባሳደሩ አድርጎ የሾመው ሲሆን፤ አርቲስቱ የቫሞስ መኖሪያ አፓርትመንቶችን ለአንድ ዓመት ያስተዋውቃል ተብሏል፡፡
በዛሬው ዕለት ከሰዓት በኋላ በ9:00 ሰዓት ላይ፣ በስካይላይት ሆቴል፣ በቫሞስ ሪል እስቴትና በአርቲስት ነጻነት ወርቅነህ መካከል የፊርማ ሥነ ስርዓት የተከናወነ ሲሆን፤ አርቲስት ነጻነት ለአንድ ዓመት 3.7 ሚሊዮን ብር እንደሚከፈለው ታውቋል፡፡
አርቲስቱ ከፊርማ ሥነ ስርዓቱ በኋላ ”ከዚህ በኋላ በቴሌቪዥን ፣ በፖስተር … ከቫሞስ ጋር ታዩኛላችሁ!” ብሏል- ፡፡
የቫሞስ ሪል እስቴት ሥራ አስኪያጅ አቶ ግርማ ዋቅሹም በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ”አርቲስት ነጻነት ቫሞስ የሚገነባቸውን የመኖሪያ አፓርትመንቶች ለማስተዋወቅ ፈቃደኛ በመሆኑ በጣም ደስተኞች ነን፤ እሱ ሸክማችንን ያቃልላል ብለን እናምናለን“ ብለዋል፡፡
በ2009 ዓ.ም ከ83 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ካፒታል የተመሰረተው ቫሞስ ትሬዲንግ ኃላ.የተ.የግ.ማኀበር፣ በሆቴልና ቱሪዝም፣ በኮንስትራክሽን፣ በሪል እስቴት ማልማትና ተጓዳኝ የንግድ ሥራዎች ላይ የተሰማራ ድርጅት ነው፡፡
ቫሞስ ሪል እስቴት፤ በለሙ አካባቢ በ2717 ካሬ ሜትር ላይ ባለሁለት መንታ የመኖሪያና የንግድ ቤት አፓርትመንት መገንባቱ ይታወቃል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.