fbpx

የጎጆ ብሪጅ 2ኛው ዙር የጤናው ዘርፍ እና መደበኛ የማህበረሰቡ የጎጆ ሮስካ እጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ተካሄደ!

2ኛው ዙር የጤናው ዘርፍ እና መደበኛ የማህበረሰቡ የጎጆ ሮስካ እጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ተካሄደ! ጳጉሜ 5/2015 ዓም በግራንድ ኤሊያ ሆቴል በተካሄድ የእጣ ማውጣት ስነ ስርዓት በጤና ዘርፍ ለ200 እድለኞች እጣ የወጣ ሲሆን በመደበኛ ሮስካ ደግሞ 300 እድለኞች የእጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ተካሄዷል።
በመደበኛ ሮስካ የሚጠበቅባቸውን ቁጠባ ቆጥበው ለእጣው ብቁ የሆኑ 7,321 ተመዝጋቢዎች ውስጥ በዛሬው እለት 300 እድለኞች እጣው የወጣ ሲሆን እና በጤና ዘርፍ 7,816 ብቁ የሆኑ ተመዝጋቢዎች ውስጥ ለ200 እድለኞች በዛሬው እጣ ወጥቷል።
ጎጆ ብሪጅ እስካሁን ስምንት የጋራ መኖሪያ ቤቶች ማህበራትን ያደራጀ ሲሆን አንዱ ማህበር ግንባታ መጀመሩ ተገልፇል። ሌሎች የክረምት ወቅት ለግንባታ መጀመር አመቺ ስላልሆነ በቀጣይ እንደሚጀምሩ ተገልፇል። በጤና ዘርፍ የወጣው የመጀመሪያው ዙር እድለኞች የማህበር ማደራጀት ስራው እየተሰራ እንደሆነ ተገልፇል።
በቀጣይ የክፍያ መቆጣጠሪያ ሶፍትዌር እየበለፀገ እንደሆነ የገለፁት የጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አልማው ጋሪ በቀጣይ ከዋጋ መጨመር ጋር ተያይዞ ጥናት እየተጠና ሲሆን መጠነኛ የዋጋ ጭማሪ እንደሚኖር ተናግሯል።

Reference: Gojo bridge housing

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.